የመመሪያ መለያ: 411/2013
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2010 ዓ.ም.
Language: Amharic

የጤና ባለሙያዎች በነጥብ ምዘና ዘዴ የድልድል አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 411/2013

ለረጅም ዓመታት ይሠራበት የነበረውን የሥራ ምደባ ዘዴን በማስቀረት አዲስ የነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴን በመጠቀም በሀገራችን ያሉ የሥራ መደቦች በተመሳሳይ መመዘኛዎች (Factors) ተመዝነው ደረጃ እና ደመወዝ እንዲወስን ለማድረግ በየሴክተር መ/ቤቶች ያለ የሥራ መደቦች የሥራ ዝርዝር የማዘጋጀት ሥራ በፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴርአስተባባሪነት መከናወኑ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሠረትም የጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ሥራ አመራር የሥራ መደቦች የሥራ ዝርዝርበነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ከወረዳ እስከ ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያሉና የተጠሪ ተቋማት የጤና ሥራ አመራር መደቦች በአራት ተዋረድ የዘርፉን ባለሙያዎችና አማካሪዎችን በማሳተፍ የሥራ ዝርዝር በማዘጋጀት እንዲመዘኑ ተደርጓል፡፡

በሀገራችን የጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ሞዴል፣ በጤና ዘርፍ አደረጃጀት፣ እንዲሁም በጤና የሰው ሀብት ስምሪትና ስኮፕ መሠረትለሁሉም የጤና ሙያዎች የትምህርት ዝግጅትን መነሻ በማድረግ ለ428 የጤና ሙያ መደቦችና ለ192 የጤና ሥራ አመራር መደቦች የሥራ ዝርዝርበማዘጋጀትና በመመዘን ከደረጃ VI እስከ XXIl ባለው ማዕቀፉ ወስጥ ተካተዋል፡፡

በመሆኑም በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ክፍተት የነበረው የባለሙያዎች ሥራ ዝርዝር አለመኖርን የሚፈታና ለመጀመሪያ ጊዜ በጤና ሙያ ዘርፎች ወጥ የሆነ የሥራ ዝርዝር (Job Discription) ማዘጋጀት ተችሏል፡፡

በዚህ መሠረትም የማነፃፀር እና ድልድል ለማድረግ እንዲረዳ ደረጃ ለወጣላቸውና ዝርዝራቸው ከታች ለተጠቀሱት የሙያ ዘርፎች ይህ የአፈፃፀም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የህዝብ አገልግሎት እና የሰው ሀብት ሚኒስቴር

Ministry of Public Service and Human Resources

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration