የመመሪያ መለያ: 455/2013
ቀን: የካቲት 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

ለግብርና ግብአት አቅርቦትና አገልግሎት ማዕከላት የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 455/2013

የተሻሻለ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና አገልግሎት ሥርዓት በሀገሪቱ ማስፋፋት ለአ/አደሮች፣ለአርብቶ አደሮች እና ለአልሚ ባለሃብቶች የግብርና ግብዓትን ተደራሽነት በማረጋገጥ ለግብርና ምርትና ምርታማነትን ዕድገት፤የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው:: በሀገራችን ለበርካታ ዓመታት ሲተገበር የቆየው የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ግብይት ሥርዓት ከፍተኛ የሆነ የመንግሥት በጀት ሲጠይቅ የቆየና የተራዘመ የግብይት ሰንስለት የነበረው ነው፡፡ ይህም የግብዓት አቅርቦቱ በሚጠበቀው ጥራት፣ መጠን፤ ጊዜ፣ ቦታ፣ ተወዳዳሪ ዋጋ፤ በተጠያቂነት እና ቀልጣፋ በሆነ አገልግሎት እንዳይከናወን አድርጎታል፡፡ አልሚ ባለሃብቱንም በበቂ ደረጃ ባሳተፈ መልኩ ያልተከናወነና የተጠቃሚውን ተደራሽነት ያላረካ ሆኖ ቆይቷል። ተጠቃሚው ከግብዓት በተጨማሪ ስለአጠቃቀሙ እና ስለ ጉዳቱ፤ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ግብዓቶች ጥቅም ላይ የዋሉ መያዣዎቻቸው አወጋገድ በባለሙያ የተደገፈ በቂ መረጃ ስለማያገኝ ለገንዘብ፣ ለጤና፤ ለአካባቢ ጥበቃና ተያያዥ ችግሮች አጋልጦታል፡፡

ይህን ችግር ከግምት በማስገባትም የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ግብይት ሃደት የተደራጀና የዘመነ ለማድረግ በቀጥታ ግብዓት ግብይት እና በአንድ ማዕከል ግብዓትን የማቅረብ ሥራ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይቷል፡፡ የተገኘውን መልካም ተሞክሮ ከግምት በማስገባት በአንድ ማዕከል ደረጃ ግብዓት ማቅረብ እና የምክር አገልግሎትን መስጠት አስራርን በማስፋት እና በማዘመን፤የግብዓት ተደራሽነትን ማረጋገጥ አስፈላጊነቱ ታምኖበታል፡፡ ስለዚህም አመቺ የሕግ ምህዳር በመዘርጋት ማዕከላት የሚያቋቁሙ ባለሃብቶችን ማበረታታት፣የግብዓት ተጠቃሚውን ፍላጎትና መብት ማስጠበቅ እና የግብዓት ተደራሽነት ማረጋግጥ እንዲያስችል ይህ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና አገልግሎት ማዕከላት ለማቋቋምና ለማስተዳደር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የግብርና ሚኒስቴር

Ministry of Agriculture

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration