የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ሲባል በሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ ምክንያት በልማት ማስፋፊያ አካባቢዎች ውስጥ የሚኖሩ አርሶ አድሮች ከይዞታቸው እንዲነሱ እየተደረገ የቆየ በመሆኑ እና ወደፊትም ከይዞታቸው የሚነሱ ስለሆነ ከይዞታቸው የተነሱና የሚነሱ ዜጎች ላይ የሚፈጠረውን መፈናቀልና ልዩ ልዩ ችግሮችን በቅድሚያ ለመከላከልና ለኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግር ተጋላጭ በመሆን የደረሰባቸውንና የሚደርስባቸውን የመልካም አስተዳደር ችግር በመቅረፍ በዘላቂነት ማቋቋም በማስፈለጉ፡፡
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተሻሻላው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 በተሰጠው የሕግ ሥልጣን መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤትን በደንብ ቁጥር 79/2008 ዓ.ም እንዲቋቋም ተደረጓል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከተቋቋመ በኋላ በደንቡ ላይ የተገለጸውን ዓለማ እና የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር መነሻ በማድረግ በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ መሠረት የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸውን በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱትን መልሶ ማቋቋም እና በቀጣይም የሚነሱ አርሶ አደሮችን ከኢኮኖሚና ማኅበራዊ ችግር ለመከላከል እና የኑሮ ሁኔታቸው እንዲሻሻል ለማድረግ በቅድሚያ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን ከኪራይ ሰብሳቢነት፤ ከመልካም አስተዳር ችግሮች እንዳይጋለጡ እንዲሁም ፍህታዊነት ግልጽነትና ተጠያቂነት ባሰፈነ መልኩ በድጋፍ መስፈርቶች፣ በድጋፍ አፈጻጸም ሂደቶች እና የድጋፍ ስርዓቶች አስመልክቶ ግልጽ በሆነ መመሪያና አሠራር መፈጸም ስላለበቸዉ ይህን የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ የድጋፍ ማዕቀፍ አፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 79/ 2008 ዓ.ም መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡