የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የልማት ድርጅቶችን ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት፤ መከታተል፣ በልማት ድርጅቶችና አክስዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥትን በመወከል የመንግሥት ባለቤትነት መብት ለማስከበርና ለመምራት የተቋቋመ ኤጀንሲ ነው፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሥራ አመራር ቦርድ ትኩረት በስትራቴጂክ ዕቅድና በድርጅቱ ተልዕኮ መሳካት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ወጥና ግልፅ በሆነ መንገድ ተጠያቂነትን (accountability) ለማስፈን የሚያስችል አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
ድርጅቱ ባስገኘው ውጤት ላይ በመመስረትና በሀገር ደረጃ እየተከሰተ ያለውን ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የሥራ አመራር ቦርዱን በማበረታታት የልማት ድርጅቱ በአገር ውስጥና በዓለም ዓቀፍ ገበያ የተወዳደሪነት መንፈስ እንዲኖገው ለማድረግ፤
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ተግባርና ኃላፊነቱን ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 445 /2011 አንቀጽ 5 (3) መሠረት ይህንን መመሪያ እሻሽሎ እውጥቷል፡፡