የመመሪያ መለያ: 344/2013
ቀን: ታህሳስ 13፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

በህይወት ባሉ ዘመዳሞች መካከል ስለሚደረግ የአካል ክፍሎች ንቅለ-ተከላ ህክምና አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 344/2013

ከበርካታ አመታት በፊት በበለፀጉት ሀገሮች የተጀሚው የንቅለ ተከላ ህክምና በሃገራችን ከአይን ብሌን ንቅለ ተከላ በስተቀር ሳይተገበር የ ቆየ ቢሆንም በአካል ክፍሎች ህመም ምክንያት ለሚቃዩ እና ለሞት ለሚዳረጉ ግለሰቦች የህክምና መፍትሄ ከመስጠት አንፃር ህክምናው እንዲዳብርና በስፋት እንዲሰጥ ለማድረግ የአሠራር መሣሪያ በሚፈለጉ፤

በሃገራችን የሕግ ስርዓት ንቅለ ተከላ የሚሄደው ለንግድ ዓላማ ካልሆነ እና የለጋሹን ጤንነት ሁኔታ ማይጎዳ መልኩ እስከተካሄደ ድረስ ንቅለ ተከላ ማካሄድ እንደሚቻል የተደነገገ በሆኑ፤

ምንም እንኳን ህክምናው የጤና አገልግሎት አካል ሆኑ በሃገራችን የተለያዩ ህጎች ተደንግጎ የ ሚገኝ እና ህጎቹም አገልግሎቱን ለማስጠት በቂ ናቸው ሊባል ቢችልም በንቅለ ተከላ ህክምና ወስጥ ሊነሱ የሚችሉ ሌሎች ጉዳዮችን ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመኘቱ፤

በሃገራችን በአሁኑ ጊዜ ንቅለ ተከላ ለማካሄድ የሚችሉ የጤና ተቋማትን መፍጠር እንደሚቻል ከግንዛቤ በማስገባት ህክምናውን በነዚሁ የጤና ተቋማት በመስጠት ዜጎች ህክምናውን ለማግኘት ወደ ሌላ አገር በመሄድ የሚወጡትን ከፍተኛ ወጪ እንዲያስቀር እንዲሁም ህክምናው ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም
ታማዊች ተደራሽ እንዲሆን ወጥ የአሠራር ስርዓት ለማርጋት፤

ከሌሎች ሃገራት ተሞክሮ የንቅለ ተከላ ህክምና አገልግሎት ለንግድ ዓላማ መዋሉን ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ ለከፍተኛ የማኅበራዊ ቀውስና የወንጀል ድርጊት የማያጋልጥ ማሆኑን በመረዳት የሰዎች የአካል ክፍሎች ለመነገጃና ለማትረፊያ እንዳይሆኑ ለመከላከል፤

ከንቅለ ተከላ ህክምና ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ የ ሰዎችን ሰብዓዊ ክብርና ማሰረታዊ ነፃነቶች የሚጋፉ ማናቸውም ከስነ ምግባር ወጪ የሆኑ ህገ ወጥ አሰራሮችን ለማከላከል፤

በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ተግባራዊ የሚደረገው የንቅለ ተከላ ህክምና የስጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ባላቸው ግለሰቦች መካከል ብቻ ማኑን ለመደንገግ፤

በንቅለ ተከላ ህክምና ተሳታፊ የሚሆኑ አካላትን ከመደበኛ ተግባርና ሃላፊነታቸው በተጨዌ ህክምና ወስጥ ተሳታፊ በመሆናቸው የሚጠበቅባቸውን ተግባርና ኃላፊነት በዝርዝር ለማስቀመጥ፤ የጤና ጥበቃ ሚስቴር በአዋጅ ቁጥር 691/2003 በአንቀጽ 10 በተሰጠው ሥልጣን ማረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡ ፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

Ministry of Health

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration