የመመሪያ መለያ: 854/2014
ቀን: ታኅሣሥ 17፥ 2015 ዓ.ም.
Language: Amharic

በዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች የሚቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 854/2014

የዱር እንስሳት ሃብት ባልተቀናጀና አግባብነት በሌለው አጠቃቀም ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነና ለአደጋ ተጋላጭነቱ እየጨመረ በመምጣቱ፤

በዱር እንስሳትና በዱር እንስሳት ውጤት ላይ የሚደረገው ንግድ የዱር እንስሳቱን አደጋ ላይ የማይጥልና ህጋዊ በሆነ መንገድ እነዲከናወን ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በዱር እንስሳት ኢ-ፍጆታዊ የአጠቃቀም ስልት አማካይነት ከዱር እንስሳት ሃብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማጎልበት ለሀገሪቱ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች በሚቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚስተዋሉ የአሠራር ክፍተቶችን በማስወገድ ወጥነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ቀደም ሲል ለወጡት የዱር እንስሳት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 541/1999 እና የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር163/2001 ማስፈጸሚያ መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፤

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር541/1999 አንቀጽ 17 (2) በተደነገገው መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

Ministry of Culture and Tourism

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration