የመመሪያ መለያ: 839 /2007
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2007 ዓ.ም.
Language: Amharic

ጥራቱ የተገለጸ ዘር ሥርዓት ማስፈጸማያ መመሪያ ቁጥር 839/2007

በኢትዮጵያ ሦስት ዋና ዋና (መደበኛ፣ ተሸጋጋሪና ኢመደበኛ) የዘር ሥርዓቶች አሉ፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት በየዓመቱ በመደበኛ የዘር ሥርዓት በኩል የሚቀርበው የዘር መጠን ከ20 በመቶኛ አይበልጥም፡፡

ነገር ግን በፍጥነት እያደገ የመጣውን የአርሶ አደሩን የምርጥ ዘር ፍላጎት በመደበኛ ሥርዓት በሚቀርበው ዘር ብቻ ማሟላት ባለመቻሉ በኢመደበኛ ስርዓት ተመርቶ የሚቀርበው ዘር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህ ዘር ግን ጥራቱን ጠብቆ ለአርሶ አደሩ ባለመቅረቡ ሃገሪቱ በምትፈልገውና በምትጠብቀው መልኩ ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል አላስቻለም፡፡

ጥራት ያለው የዘር አቅርቦት ለምርትና ምርታማነት ማደግና ብሎም ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት አስፈላጊ በመሆኑና ይህ ደግሞ በአንድ ጊዜ ለሁሉም አርሶ አደር ማዳረስ ቀላል ባለመሆኑ አርሶ አደሮች እንደ አቅማቸው በተለያየ ደረጃ የሚገኝ የዘር ጥራት እየተጠቀሙ በሂደት ከፍተኛ ጥራት ያለውን ዘር መጠቀም ወደሚችሉበት ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል ሥርዓት መቀየስ በማስፈለጉ ምክንያት በዘር አዋጁ መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የግብርና ሚኒስቴር

Ministry of Agriculture

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration