የመመሪያ መለያ: 588/2013
ቀን: ጥር 25፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ የኢደ ምልክት ፍቃድ አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 588/2013

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ምልክት ከዚህ በኋላ “የኢደ ምልክት” ተብሎ የሚጠቀሰው አንድ ምርት የተወሰነ የኢትዮጵያ ደረጃን ተፈላጊ ሁኔታዎች እና ሚመለከተውን ደንብ ወይም መመሪያ የሚያሟላ መሆኑን እና በዚህ መመሪያና በሚያረጋግጠው አካል መመሪያዎች ውስጥ በተገለፀው መሠረት ለተስማሚነት ምዘና መመሪያዎች ተገዢ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ይኽም ምርቱ ተፈላጊ ሁኔታዎችን እንዲያሟላ በማድረግና ተአማኒነትን በመፍጠር በአገር ውስጥና በአለምአቀፍ ገበያ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ምልክቱ የሚያገለግለው አግባብነት ካለው የኢትዮጵያ ደረጃ ወይም በሚያረጋግጠው አካል ደንብ እና ተያያዥነት ያላቸው የማረጋገጫ ተፈላጊ ሁኔታዎች ውስጥ ከተጠቀሰ የኢትዮጵያ ደረጃ ጋር ለሚጣጣሙ ምርቶች ብቻ ነው፡፡

በዚህ ሰነድ ውስጥ የተገለፀው የኢደ ምልክት አጠቃቀም መመሪያ በደንብ ቁጥር193/2003 አንቀጽ 5 እና 14 መሠረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ቀደም ሲል ምልክቱ አስገዳጅ ደረጃ ለነበራቸው ምርቶች ብቻ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ነገርግን ይህ መመሪያ ሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በፍቃደኝነት እና በአስገዳጅነት ተፈፃሚ ለሆኑ የምርት ደረጃዎች ያገለግላል፡፡ በአምራቹ በኩል የኢደ ምልክት በምርቶች ላይ የሚደረገው ምርቱ አግባብነት ያላቸውን የኢትዮጵያ ደረጃዎችና የቴክኒክደንቦችን በሙሉ ስለማሟላቱ ለመግለፅ ሲሆን በተስማሚነት ምዘና አካል ደግሞ ምርቱ ደረጃውን ስለማሟላቱ መረጋገጡን ለማሳየት ነው፡፡የተስማሚነት ማረጋገጫ ማመልከቻ ለኢደ ምልክት አጠቃቀም ሲቀርብ ማመልከቻው ምርቱ ማሟላት የሚገባውን የምርት ደረጃ መስፈርት እና ተስማሚነቱን ለማረጋገጥ መሠረት የተደረገባቸውን ሌሎች መመሪያዎች ወይም ደንቦችን የያዘ ይሆናል፡፡

ይህ መመሪያ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ምልክትን (የኢደ ምልክት) በሁሉም የህትመትና የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ላይ ለመጠቀም አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ መረጃዎችን ይሰጣል፡፡ ይህ መመሪያ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ምልክት ባለበት ሁኔታ ተጠብቆ እንዲቆይና ለሕዝብ እንዲታወቅ ይረዳል፡፡ በሰርተፊኬት ሰጪው አካል በኤሌክትሮኒክመልክ የሚሰጥን የኢደ ምልክት አቀማመጥም ሆነ መጠን በዚህ መመሪያ አንቀጽ 8 በተገለፀው መሠረት ካልሆነ በስተቀር በምንም አይነት የጥበብ ሥራ መለዋወጥ አይቻልም፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ

Institute of Ethiopian Standard

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration