የመመሪያ መለያ: 25/2012
ቀን: ነሀሴ 7፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅትን፣ የአደራ በጎ አድራጎት ድርጅትና የበጎ አድራጎት ተቋምን ለማቋቋም የወጣ መመሪያ ቁጥር 25/2012

በማህበር መልክ መደራጀት ሣይኖርባቸው ገንዘባቸውንና ንብረታቸውን በመለገስ ለብቻቸው ወይም በተናጠል በመሆን በአደረጃጀቱ ያልተወሣሠበና ቀላል የአስተዳደር ስልትን የሚከተል የበጎ አራጎት ድርጅት ዓይነት በማቋቋም የበጎ አድራጎት ሥራ መሥራት የሚፈልጉ ሰዎችን መደገፍ፣ ማበረታታትና ለሥራቸውም ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና የአደራ የበጎ አድራጎት ድርጅትን ለማቋቋም መነሻ ገንዘብ ወይም ንብረት ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ መስጠት ሕግ የሚያስገድድ ሲሆን ይህንኑ አነስተኛ መነሻ የገንዘብ መጠን በሕግ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤

የበጐ አድራጐት ተቋም ከፈረሰ በኋላ የድርጅቱ ገንዘብና ንብረት ድርጅቱ ያሉበትን ወጪዎችና ዕዳዎች ለመሸፈን በቂ ሆኖ ካልተገኘ ወጪዎቹንና ዕዳዎቹን ለመክፈል የሚያስችል የዋስትና ገንዘብ ወይም ንብረት ድርጅቱ ሲቋቋም የድርጅቱ መሥራች አባላት ማስያዝ ስለሚኖርባቸው ይህንኑ አነስተኛ የዋስትና የገንዘብ መጠን በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 በአንቀጽ 9 (4) እና አንቀጽ 28 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ

F.D.R.E Agency for Charitable Organizations and Associations

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration