የመመሪያ መለያ: 431/2013
ቀን: ታህሳስ 20፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

ስደተኞች ከስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ውጭ የሚንቀሳቀሱበትና የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 431/2013

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ስደተኞችን ተቀብላ ባፀደቀቻቸዉ የስደተኞችን ጉዳይ በሚገዙ አለም ዓቀፍና አህጉር ዓቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ መርሆች ጋር ተጣጥሞ እንደ አዲስ በወጣው የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1110/2011 መሠረት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ከለላና ሰብዓዊ ድጋፍ እየሰጠች ትገኛለች፡፡

በአዲስ የጸደቀው የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለውጪ አገር ዜጎች በአጠቃላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈፃሚ የሚሆኑ ህጎች እንደተጠበቁ ሆነው በመረጡት የአገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት ነጻነት አላቸው፡፡በተጨማሪም ይህንን መሠረታዊ መብት ለማስተግበር የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ስደተኞቹ ወይም ጥገኝነት ጠያቂዎቹ የሚኖሩባቸውን ቦታዎችና አካባቢዎች ለማመቻቸት እንዲሁም ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብታቸውን እንዲጠቀሙ ለማስቻል ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚችል ይደነግጋል፡፡

በዚህ መሠረት ስደተኞች ከተረጂነት ተላቀዉ ራሳቸዉን የሚችሉበትና ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙበትን እድል ለማስፋት ከሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች መካከል በኤጀንሲዉ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘዉ ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያ ዉጪ የሚንቀሳቀሱበት፣ በመደበኛነት መኖር የሚያስችላቸዉ ሁኔታ (Out of Camp Policy /OCP/) እንዲሁም ድጋፍ እያገኙ በከተማ ስደተኝነት የሚኖሩበት (Urban Assisted) ሁኔታዎች ይገኙበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስደተኞች በካምኘ ብቻ ታጥረው መኖር ሳይጠበቅባቸው ሕጋዊ አሠራርን ተከትለው በአገሪቷ ውስጥ በሚፈጠሩ የተለያዩ የሥራ እድሎችን ለመጠቀምና ሕይወታቸውን ለመቀየር ሲፈልጉ ከካምኘ ውጪ የመኖር እድል እንዲሰጣቸው በማሰብ ከዚህ ቀደም የነበረው ስደተኞችን ከካምኘ ውጪ እንዲኖሩ የሚፈቅደው አሠራር እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ወጥ በሆነና ከስደተኛ ኮንቬንሽንና፣ የስደተኞች ጉዳይ አዋጅና ተዛማጅ አለማ አቀፍ መርሆዎች ጋር በተጣጣ መመልኩ የአሠራርን ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት

FDRE Refugees and Returnees Service

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration