የመመሪያ መለያ: 433/2013
ቀን: ታህሳስ 20፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የስደተኞች ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ መመሪያ ቁጥር 433/2013

በኢፌድሪ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ተቀጣሪ ወይም ተሿሚ የሆነ ሠራተኛ/ኃላፊ የኤጀንሲውን ፖሊሲና አቅጣጫዎች በቅልጥፍናና በውጤታማነት የመፈጸምና ለስደተኞችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከመንግሥትና ከአጋር አካላት የሚቀርቡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በመልካም ስነ-ምግባር፣ በቅንነት፣ በታማኝነትና በጥራት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡

በኤጀንሲውና በአጋር አካላት ለስደተኛውና ስደተኞችን ላስጠለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚሰጡ አገልግሎቶች በተቀመጠላቸው የአገልግሎት ስታንዳርድ መሠረት ባለመሰጠታቸው ምክንያት እርካታ ያላገኙ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ቅሬታና አቤቱታ የማቅረብ፣ ተገቢውን ምላሽ የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ እና ኤጀንሲውም ከስደተኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን ተቀብሎ በተቀላጠፈ ሁኔታ የመፍታት ግዴታ ስላለበት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በየደረጃው ባሉ የኤጀንሲው መዋቅሮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን ለመፍታት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈልጓል፡፡

በመሆኑም የኢፌድሪ የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1110/2011 ላይ የስደተኞች አጠቃላይ መብቶችና ግዴታዎችን ባስቀመጠው መሠረት፣ ኤጀንሲው ለስደተኞች የሚያደርገውን የአገልግሎት አሰጣጥ በቀጣይነት የሚሻሻልበትን ስልት ለመቀየስ፤ ተግባራዊነቱንም ለመከታተልና ለመገምገም፤ የአገልግሎት አሰጣጡን በስታንዳርዱ መሠረት ለማድረግና በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት ለሚያጋጥሙ የአሠራር ግድፈቶች የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት ለመዘርጋትና ተግባራዊ ለማድረግ ይህን “የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት

FDRE Refugees and Returnees Service

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration