በከተማው ውስጥ የሚገኘውን የከርሰ ምድር ውሃ ሃብት ፍትሃዊና ዘላቂ በሆነ መንገድ በማልማት ጥቅም ላይ እንዲውል ለማስቻል ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚ ደንበኞች የራሳቸውን አማራጭ የውሃ መገኛ እንዲያጎለብቱ እና እንዲጠቀሙ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በከተማው ውስጥ የራሳቸውን የውሃ ጉድጓድ አዘጋጅተው እየተጠቀሙ ያሉ እንዲሁም በራሳቸው ተነሳሽነት የጉድጓድ ቁፋሮ ፍቃድ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሰዎች ፍቃድ መስጠት፣ ቁፋሮውን አጠናቀው ከጨረሱ በኋላ የአጠቃቀም ፍቃድ ለመስጠትና በቂ ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ በማስፈለጉ፤
በከተማው ውስጥ የሚቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶች ደረጃቸውን የጠበቁና ውስን የከርሰ ምድርሀብቱን መጠን በማይጎዳ መልኩ ሥራ ላይ ለማዋልና በቁፋሮና አጠቃቀም ጉድለት ምክንያት የሀብት ብክነት መቀነስ በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 16(2) (ሠ) እና 16(20) (መ)መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡