የሰብል ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ምርጥ ዘር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ብዙ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ መንግሥትም ይህን በመገንዘብ ለምርጥ ዘር አቅርቦት ትኩረት በመስጠት የፖለስ ምህዳርን በማመቻቸት የተጠቃሚውን የምርጥ ዘር ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከዝርያ ማፍለቅ አስክ ተመስከረለት ዘር ማምረት ድረስ ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዝርያ መዝገብ ከተመዘገበ የሰብልና የመና ዝርያዎች መካከል ከ85% በላይ የሚሆነት የመንግሥት ሃብት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ለሰብልና መና ምርምር እና ለመነሻ ዘር ብዜት ትኩረት በመስጠት በመሰረተ ልማት፣ በሎጂስቲክ እና በሰው ኃይል አቅም ግንባታ ረገድ ከፍተኛ ሃብት ወጪ ሆኖ ሲሰራበት ቆይቷል፡፡
ከፍፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ቢፈስም የመነሻ ዘር አቅርቦት እና ሥርጭት በተማከለ የመረጃ ልውውጥ ክፍተት፣ በአቅም ውስንነት፣ ባልተቀናጀ ዘር ማምረትና ስርጭት፥ በጥራት ጉድለት እና ፍትሃዊ ሃብት ደግሞ በዘርፉ ለተሰማሩ ሀጋዊ አምራቾች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እየቀረበ አይደለም፡፡ ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው ለተፈላጊ የስብልና የመና ዝርያዎች በሚፈለገው መጠንና ጥራት የመነሻ ዘር ተባዝቶ ያለመገኘቱ በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት እና አገር አቀፍ የሆነ የመነሻ ዘር አቅርቦት አቅምን ለመገንባት የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መመርያ ተዘጋጅቷል፡፡