ኤጀንሲው የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስና ለጡረታ ባለመብቶች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአሠራር ስልት መቀየስ አስፈላጊ በመሆኑ፣
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችንና ሠራተኞችን ምዝገባና ማስረጃ አደራጅቶ መያዝ የጡረታ አበል ውሳኔ ሥራ በተቀለጠፈ ሁኔታ እንዲፈጻም ስለሚያደርግ፣
የጡረታ አበል ለመወሰን የሚያስፈልጉ ዝርዝር ማስረጃዎችን ለፈጻሚው ግልጽ ማድረግ ስለሚያስፈልግ፣
በተለያዩ ጊዜያት የወጡ መመሪያዎችን ማጠቃለልና ከመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 እና ከመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁ/907/2007 ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ማስተካከል ስለሚገባ፣
በመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 60(2) ለኤጀንሲው በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚከተለው የመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ ሥራ አፈጻጸም መመሪያ ወጥቷል፡፡