1.1 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የውጭ ምንዛሪ ያስተዳድራል፡ ፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባንኩ የውጭ ምንዛሪ አቅምን ለማጎልበት የሚረዱ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ወርቅ የውጭ ምንዛሪ ማከማቻ አንዱ ሀብት እንደመሆኑ መጠን ከአገር ውስጥ አቅራቢ ድርጅቶች በመግዛት እና ወደ ውጭ አጓጉዞ በመሸጥ ወይም በውጭባንኮች (Correspondent banks) ውስጥ አስቀምጦ በማበደር ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ወይም ግኝት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ባንኩ ባለፉት ዓመታት ሰፊ ጥረት አድርጓል፡፡ አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
1.2 ይሁንና በሀገሪቱ በተለምዶአዊ አሠራር ወርቅ የሚያመርቱ ማህበራት/ግለሰብ ነጋዴዎች በርካታ ቢሆኑም ሁሉም የሚያመርቱትን ወርቅ ሕጋዊ በሆነ መልክ ለባንኩ አቅርበው አይሸጡም፡ ፡ በባህላዊ የወርቅ ምርት በሚሰተዋሉ በርካታ ችግሮች ምክንያት ከዘርፉ መገ ኘት የነ በረበት የውጭ ምንዛሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ገቢዎች ከሚጠበቀው በታች እየወረዱ በመምጣታቸው እንደአገር የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት አልተቻለም፡፡ ከሌሎች ችግሮች በተጨማሪ ለአቅራቢዎች የሚከፈለው ማበረታቻ ተወዳዳሪ ባለመሆኑ ለባንኩ መቅረብየ ነ በረበት ወርቅ በሕገወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ ገበያ እንዲሸጥ አንዱ ምንክያት መሆኑ በተደረገው ጥናት ተረጋግጧል፡፡
1.3 ከዚህ ዘርፍ የሚገኘው ሐብት በአግባቡ ለአገር ጥቅም ለማዋል እና አምራች ድርጅቶች ሕጋዊ በሆነ አካሄድ እንዲበረታቱ ለማድረግ የወርቅ ሽያጭ እና ክፍያ አፈጻጸም በአግባቡ የሚመራበት ደንብ ቁጥር GT/001/2008 ቀደም ሲል በባንኩ ተሻሽሎ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ በዚሁ ደንብ መሠረት አምራች
ማህበራት እና ግለሰብ ነጋዴዎች ወርቅ ለባንኩ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ የወርቅ አቅርቦት በማሻሻል ከባህላዊ የወርቅ ዘርፍ የሚገኘውን የውጭምንዛሪ ማሳደግ እንዲቻል መንግሥት አቅራቢዎችን በማበረታታት ከዘርፉ መገኘት የሚገባውን አገራዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ወስኗል፡፡
1.4 በመሆኑም፤ ከላይ በተራ ቁጥር (1.3) የተጠቀሰውን ለመተግበረ በማዕከልም ሆነ በውክልና የወርቅ ግዥ የሚከናወኑ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎችም ሆኑ ብሔራዊ ባንክ የሚመራበትን አዲስ የማበረታቻ ዋጋን ጨምሮ የወርቅ ግዥ የሥራ ሂደት አፈጻጸም፣ ክምችት እና ርክክብ አፈጻጸም የሥራ ሂደት (Procedure Manual) እንደሚከተለውተሻሽሏል፡፡