በሀገራት መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚያጠናክሩ ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች ላይሀገሪቱን የሚወክሉ እና የሚያስተዋውቁ ባህላዊ ምርቶችና አገልግሎቶች በመለዋወጥ የባህል ዲፕሎማሲን ማሳደግ በማስፈለጉ፣
የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርሶች እና ዕሴቶች በተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ የግንኙነት መድረኮች በማስተዋወቅ፤ ሀገራዊ ገፅታን መገንባት በማስፈለጉ፤
ሚኒስቴሩ ከተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የሀገራት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ ኢንቨስተሮች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር የሚያደርጋቸውን የአጋርነት ግንኙነቶች ለማጠናከር የስጦታ አሰጣጥ አሠራር ሥርዓትን መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በሀገራችን ህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር የባህል ለባህል ልውውጦችን በማካሄድ ማኅበራዊ ትስስርን ማጠናከር በማስፈለጉ፡፡
ከሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ጋር የሚጣጣም ወጥ፣ ግልፅና ፍትሐዊ የስጦታ አሠጣጥ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ግንኙነት እንዲያደርግባቸው በሕግ የተፈቀዱ ተግባራትን ለማከናን ይህንን መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡