ሀገራችን ኢትዮጵያ የዜጎችን ፍትሐዊ የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፖሊሲ ቀርጻ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ስታከናውን ቆይታለች፡ ከነዚህም ስራዎች ውስጥ በውጭ ሀገር የሚኖሩ አትጵያዊያን የሚማሩበት የማህበረስብ ት/ቤት ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የውጭ ሀገር ዜጎች የሚማሩበት የማህበረስብ ት/ቤት፣ በውጭ ሀገር ባለሃብቶች የሚቋቋሙ ት/ቤቶችና ዓለም አቀፍ ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ፍትሐዊ የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ማሳያዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም በነዚህ ት/ቤቶች ውስጥ የሚማሩ የተማሪ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ከት ቤቱ ጋር ተቀራርበው በሚኖራቸው ተሳትፎ ተገቢ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ በማስፈለጉ፤
የወላጆች፣ተማሪዎች፣መምህራንና እና ባለድርሻ አካላት በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ መሳተፍ ጤናማና ፍትሐዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑ ስለታመነበትና ይህ ስራ የሚመራበት የአሠራር ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የተማሪ ወላጆች ተማሪዎች መምህራንና ባለድርሻ አካላት በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻልና በመማር ማስተማር ሂደት ወቅት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ይቻል ዘንድ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 34 (ሀ) መሠረት የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ት/ቤቶች የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት አደረጃጀትና አሠራር መመሪያ አውጥቷል፡፡