ለምግብነት እንዲሁም ለምግብ ማምረቻ ፋብሪካዎች የሚቀርብ ጨው በሀገራዊ ደረጃው ላይ የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ እና የአዮዲን ይዘት ጠብቆ መድረሱን ለማረጋገጥ፤
ከአዮዲን ንጥረ ነገር እጥረት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ለመከላከል፣ በምግብ ጨው ማምረት፣ ማሸግ፣ መላክ፣ ማስመጣት እና ጅምላ ማከፋፈል ንግድ ሥራ ላይ የሚሰማራ ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71 (2) መሠረት ይህ በአዮዲን የበለጸገ የምግብ ጨው ቁጥጥር መመሪያ ወጥቷል፡፡