ለህብረተሰቡ የሚቀርብ ምግብ ደኅንነት ለማረጋገጥ በምግብ ምዝገባና ፈቃድ ላይ ያተኮረ ጠንካራ እና ውጤታማ የምግብ ደኅንነት ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በሀገራችን ተመርተውም ሆነ ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምግቦች ለህብረተሰቡ ምግብነት አገልግሎት ከመዋላቸው በፊት ምንጫቸው አውቆ፤ ጥራታቸውንና ደህንነታቸውን በማረጋገጥ የገበያ ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ህብረተሰቡ ለገበያ የሚቀርቡ ምግቦች ምንጫቸውን በማወቅ ህጋዊ የሆኑ ምግቦችን ህጋዊ ካልሆኑ ምግቦች የሚለይበት በቂ መረጃ እንዲያገኝ እና ህገ-ወጥ የምግብ ንግድ ዝውውር ለመቆጣጣር የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመረጃ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ፤
በሕገ-ወጥ ምግብ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የጤና ችግር ከወዲሁ ለመከላከል እና የምግብ ደኅንነት ችግር ከማጋጠሙና በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትና አሰቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71(2) መሠረት ይህ መመርያ ወጥቷል፡፡