የምግብ ማስታወቂያ ስራ በሥርዓት ካልተመራ የሕብረተሰብን ጤና ሊጎዳ የሚችል በመሆኑ፤ የምግብ ማስታወቂያ ደረጃውን የጠበቀና ተአማኒነት ባለው መንገድ እንዲመራ በማስፈለጉ፤
የማስታወቂያ ወኪሎች፣ የማስታወቂያ አሰራጮች እና የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን የሚያሰራጩትን የምግብ ማስታወቂያ በሚመለከት በመመሪያ መወሰን በማስፈለጉ፤
የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀጽ 55 (3) እና በደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 98 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህ የምግብ ማስተዋወቅ ቁጥጥር መመሪያ ወጥቷል፡፡