በምግብ ማምረት ስራ ላይ የሚሰማሩ ድርጅቶች የሚያመርቱት ምግብ ጥራትና ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምግብ ማምረቻ ተቋማት የቅድመ ፈቃድ መስፈርት ማዘጋጀት በማስፈጉ፤
በሀገሪቱ ውስጥ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የምግብ አምራች ድርጅቶችን ያማከለ የምግብ ማምረቻ ተቋማት የቅድመ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ በማስፈለጉ፤
ከዚህ በፊት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው የምግብ አምራቾች ቅድመ ፈቃድ መመሪያ ጥቅልና የምግቦችን ባህሪ እና የአምራቹን ሁኔታ ያለገናዘበ በመሆኑ፣ አሁን ካለው የሀገራችን የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ጋር ተመጋጋቢ የቁጥጥር አሠራር ሥርዓቱን ማዘመን በማስፈለጉ፣ ለውስጥ ጥራት ቁጥጥርና የምርት ምዝገባ ስርዓት ዝርጋታን ሊሸከሙ የሚችሉ መስፈርቶችን ያላገናዘበ በመሆኑ፣ የሚጠየቁት መስፈርቶች ከምርት ጥራትና ደኅንነት ማረጋገጥ ጋር በቀጥታ ቁርኝት ያላቸው እና በሳይንስ የተረጋገጡ መሆናቸው ታሳቢ ያደረጉ ባለመሆናቸው፣ መንግሥት የዘረጋውን ምቹ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚደግፍ እና የድርጅቶችን የማምረት አቅም ታሳቢ ያደረገ መስፈርት አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ በማስፈልጉ፣
በምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀጽ 55 (3) እና በምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 4(1) መሠረት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው የምግብ ማምረቻ ተቋማት የቅድመ ፈቃድ መመሪያ ተሻሽሎ በዚህ መመሪያ ተተክቷል፡፡