በምግብ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩና የሚሰማሩ ድርጅቶች የሚልኩት፣ የሚያስመጡት ወይም የሚያከፋፍሉትን ምግብ ጥራትና ደህንነቱን በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ጤና መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምግቦች ጥራታቸውንና ደህንነታቸው የተረጋገጠ እና አግባብ ያለውን መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የአሠራር ግልፅነትና ተጠያቂነት ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡
ማንኛውም በምግብ ንግድ ስራ ላይ ለሚሰማራ ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2002 አንቀጽ 55 (3) እና የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 98 መሠረት ይህ የምግብ ላኪ፣ አስመጪና ጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶች ቁጥጥር መመሪያ ወጥቷል፡