በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የወጣ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አከናዋኝ የንግድ ሥራ ፈቃድ ለመስጠት እና ብቃትን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 802/2013 ላይ በፎብ የግዢ ሥርዓት ለሚጓጓዙ ጭነቶች የመልቲሞዳል ትራንስፖርት አከናዋኝ የብቃት ማረጋገጫና የንግድ የሥራ ፍቃድ አሰጣጥ፣ በመመሪያው የተደነገገ መሆኑና ይህን ተከትሎ ፍቃድ የተሰጣቸው አከናዋኞች አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤
በፎብ የግዢ ሥርዓት የሚገደዱና የማይገደዱ የገቢ ጭነት አይነቶችን እና አስመጪዎችን መወሰን እንዲሁም በፎብ የግዢ ሥርዓት ለሚጓጓዙ ጭነቶች በመልቲሞዳል ትራንስፖርት አከናዋኞች የሚሰጠው አገልግሎትና የአገልግሎት ዋጋን መቆጣጠርና የዌቨር ሥርዓትን በማዕከላዊነት ማስተዳደር በማስፈለጉ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዝያ 29/2012 ባደረገው 20ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ባፀደቀው የሎጂስቲክስ ዘርፍ ፖሊሲ መሠረት በሥራ ላይ ያለውን የፎብ አሠራርና አሰያየም እንዲሻሻል የተወሰነ በመሆኑ፤
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር549/1999 አንቀጽ 18(ለ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡
WHEREAS, the multimodal transport operators commercial licensing & competency certification directive no 802/2021 issued by the Ministry of Transport & Logistics deals partly with the nomination of carriers for imports concluded on FOB term. Following this it has become essential to determine the condition and service area of the carriers licensed to transport imports concluded onFOB term.
WHEREAS, the need to decide import shipments and importers that must and must not be obliged to import on FOB term and centrally manage and monitor the waiver system, the service level and service fee of carriers licensed to transport shipments obliged to be imported on FOB term.
WHEREAS, it has been decided by the council of Minsters to review the existing FOB system including nomination of carriers at its extraordinary session held on May 7, 2020. NOW THEREFORE, the Ministry of Transport & Logistics, in accordance with the powers vested in it through Article 18 (b) of the proclamation no 549/2007, has issued this directive