የመመሪያ መለያ: 452/2013
ቀን: ግንቦት 1፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 452/2013

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 398/2009 የተቋቋመ በኋላም በደንብ ቁጥር 427/2010 በወጣዉ ማሻሻያ የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ድርጅት እንደመሆኑ ተልዕኮውን ለማሣካት የሚያስችል ዘመናዊ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣

የኮረፖሬሽኑ ሃብት በሚገባ መመዝገቡን፣ መጠበቁንና በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተቀባይነት ያለው የሂሳብ አሠራርና አግባብ ያላቸው አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ አስፈላጊ የሂሳብ መዛግብት በመያዝ በኮርፖሬሽኑ አሠራር ላይ በቂ ቁጥጥር እንዲኖር የሚያደርግ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣

የኮርፖሬሽኑን ራዕይና ዓላማ ከዳር ለማድረስ እና የኮርፖሬሽኑን ዕድገትና ትርፋማነት ቀጣይና አስተማማኝ ለማድረግ የፋይናንስ አስተዳደር ሥራን በዕቅድ መምራት አስፈላጊ በመሆኑ ፣

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የመንግሥት ተቋም እንደመሆኑ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓቱ የፌደራል መንግሥት የፋይናንስ እስተዳደር ሕግ እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሂሣብ ሥራ ሕግን በማገናዘብ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ፣

የኮርፖሬሽኑን የኢንቨስትመንት አቅም ሊያሳድጉ የሚችሉ የፋይናንስ ምንጮችን ለመለየትና አዋጭነታቸውን ለማየት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት፣ የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተደደር፣ እንዲሁም የፋይናንስ መረጃንና የንብረት አያያዝ ሥርዓት አካቶ የያዘ የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል በማስፈለጉ፤

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/84 አንቀጽ 14 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

Federal Housing Corporation

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration