የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በሕግ መሠረት ይቅርታ እንደሚያደርግ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 71/7/ የተደነገገ በመሆኑ፤
የይቅርታ አሰጣጥ አፈፃፀም ሥነሥርዓት አዋጅ ቁጥር 395/1996 መሠረት ሲሰራበት የነበረውን የበለጠ ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ ሲሰራበት የቆየው የሕግ አፈጻጸም ወቅት የተገኙ ልምዶችን መሠረት በማድረግ አዋጅ ቁጥር 840/2006 በመደንገጉ እና፤
ለይቅርታ ቦርድ የሚቀርቡትን የይቅርታ ጥያቄዎች በተፋጠነ መልኩ ለማስተናገድ ይቻል ዘንድ የይቅርታ ጥያቄ ማመልከቻዎች አሟልተው መያዝ የሚገባቸውን መረጃዎች ለአመልካቾች ከወዲሁ በግልጽ ማሳወቅ ፣ ታራሚዎችን የሚመለከት አስተያየት፣መረጃና ምስክርነት ከሚሰጡ ተቋማትና ግለሰቦች የሚፈለገውን ዝርዝር መረጃ በቅድሚያ ማሳወቅ እና የቦርድ አባላትም አዋጁን በአግባቡ ለማስፈፀም የሚያስችላቸውን ሥርዓት መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የይቅርታ ቦርድ ይህን የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት መመሪያ በይቅርታ ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 840/2006 አንቀጽ 28/2/ መሠረት አውጥቷል፡፡