ከመደበኛ የስራ ቦታ ውጪ የሰነድ ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጣቸውን ተገልጋዮች በግልፅ ለይቶ በማስቀመጥ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና አገልግሎት የሚሰጥበትን አግባብ በግልፅ መደንገግ በማስፈለጉ፤
አገልግሎት አሰጣጡ ተጠያቂነት ያለው በማድረግ ላልተገባ አሠራር ተጋላጭ እንዳይሆን መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ፤
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሰነዶችን ስለማረጋገጥና መመዝገብ አዋጅ ቁጥር 922/08 አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡