የመመሪያ መለያ: 225/2013
ቀን: ሰኔ 20፥ 2005 ዓ.ም.
Language: Amharic
Sector: Export

ወደ ውጭ የሚላኩ የሆርቲካልቸር ምርቶች የትራንስፖርት ወጪ ድጐማ መመሪያ ቁጥር 225/2013

በእድገትና ትራንስፎርሜሸን ዕቅድ የተቀመጠውን የ 11 በመቶ አማካይ አመታዊ የኢኮኖሚ እድገት ግብ ለማሳካት በሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ከአበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬና ኸርብስ ኤክስፖርት የሚገኘወን አመታዊ ገቢ ከ201.7 ሚሊዮን ወደ 1,483 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማደግ የታቀደ በመሆኑ፣

በአዲስ መስመር ይህንን የሆልቲካልቸር ልማት ግብ ለማሳካት የገበያ፣ የሎጂስቲክና የትራንስፖርት ችግሮችን በመፍታት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ፣

የአበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬና ኸርብስ ምርት ውጠቶችን ከመቀሌና ባህር ዳር የማጓጓዣ ወጪ ከአዲስ አበባ የኤክስፖርት ማጓጓዣ ወጪ ጋር የሚመጣጠን ያለመሆኑ በሁለቱ ክልሎች አበባ፣አትክልት፣ ፍራፍሬና ኸርብስ አምርተው ወደ ውጪ የሚልኩ ባለሀብቶች በውጪ ገበያ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ አሉታዊ ተፅዕኖ የፈጠረ በመሆኑ፣

ይህንን ችግር በማቃለል በሁለቱ ክልሎች በሆርቲካልቸር ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶችን ለመደገፍ በአዲስ አበባ እና በሁለቱ ክልሎች መካከል የሚታየውን የሆርቲካልቸር ምርቶች የአየር ትራንስፖርት ታሪፍ ልዩነት በመደጎም የትራንስፖርት ወጪውን ተመሳሳይ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የገንዘብ ሚኒስቴር

Ministry of Finance

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration