በሃገራችን የተጠናከረ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አሠራር መኖር ፍትሃዊ የንግድ ውድድርን በማስፈን የንግዱ ማኅበረሰብ መልካም ስምን ዝናውን ጠብቆ በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ከማስቻሉም በላይ በህገወጥ መንገድ በገበያ ላይ መሳከርን በመፍጠር ተገቢ ያልሆነ ጥቀም ለማንነቱ የሚፈለጉትን አካላት በማከም የሸማቾችን ጥስም የግስበትና የውጭ ኢንስትመንትን በመሳብ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡
ይህንን ዓላማ ለማሳካት ያስችል ዘንድ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 01/1998 የወጣ ቢሆንም አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ደንብ ባለመውጣቱ አስከአሁን አዋጁን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም፡፡ በተጨማሪም በአዋጁ ኣንቀጽ 46(1) መሠረት አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተቀመጡ የንግድ ምልክቶች አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ እንደገና መመዝገብ እንዳለባቸው ቢደነግግም የማስፈጸሚያ ደንቡ ባለመውጣቱ ምክንያት እንደገና ምዝገባው አስክአሁን ተግባራዊ መሆን አልቻለም። በመሆኑም አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተቀመጡ ንግድ ምልክቶች ከዚህ ሕግ ድንጋጌ አኳያ ሲታይ ህጋዊ ጥበቃ የላቸውም ብሎ ለመከራከር በር ይከፍታል ። በተጨማሪም አዋጁ ከወጣ በኋላ የተመዘገበ የንግድ ምልክቶችም ቢሆኑ በአዋጁ በተቀመጠው የጥበቃ ጊዜ መሠረት የተመዘገቡ ባለመሆናቸው አዋጁንና ደንቡን መሠረት አድርጎ ተመዝግበዋል ማለት አይቻልም።
በመሆኑም አዋጁን ለማስፈጸም የሚያስችለው ማስፈጸሚያ ደንብ 273/2005 በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቶ ተግባራዊ በመሆነ አዋጁንና ይህን ደንብ መሠረት በማድረግ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተመዘገቡ ሁሉንም የንግድ ምልክቶች እንደገና መመዝገብ የግድ የሚል ሲሆን አዋጁ ከወጣ በኋላ የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶችንም ቢሆን በአዋጁ በተቀመጠው ጊዜና በደንቡ የተመላከቱ ጉዳዮችን ያካተተ የምዝገባ ሰርተፊኬት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ በደንቡ አንቀጽ 59 መሠረት ጽ/ቤቱ ማስፈጸሚያ መመሪያ ለማውጣት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የንግድ ምልክት ምዝገባ የሚመራበት ይህን ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አዘጋጅል::