የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ አተማመን በጉምሩክ አዋጅ ከተደነገጉ መርሆዎችና ዘዴዎች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ፣ የጉምሩክ ዋጋ አተማመን ሥርዓት በተሻለ ደረጃ ዘመናዊ፣ ግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች በወጥነት ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፣
የኮሚሽኑ የሥራ ክፍሎች፣ ቅ/ጽ/ቤቶች እና የጉምሩክ ኦፊሰሮች ከዋጋ አተማመን ጋር በተያያዘ የሚጠበቅባቸውን ተግባርና ኃላፊነት መወሰን በማስፈለጉ፣ አስመጪዎች ወይም ወኪሎቻቸው በዋጋ አተማመን ረገድ የሚኖራቸውን መብትና የተጣለባቸውን ግዴታ ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06(እንደተሻሻለው) አንቀጽ 180 (2) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡