ባለሥልጣን መ/ቤቱ በፍትሕ አካላት ፊት የሚያቀርባቸውን ክሶችና አቤቱታዎች በማስረጃ አስደግፎ ሙግት ማካሄድ ለውጤት ማብቃቱ የሚታወቅ በመሆኑ፤
የሚቀርቡት ክሶች በማስረጃ ጉድለት ምክንያት በሚሰጥ ፍርድ ባለሥልጣን መ/ቤቱ መብትና ጥቅሙን እንዳያጣ እና የባለስልጣኑን በፍትሕ አካላት ዘንድ የሚቀርብበትን ማንኛውም አይነት ክሶችና አቤቱታዎች በአግባቡ እንዲከላከል እንዲሁም የባለስልጣኑን መብትና ጥቅም በአግባቡ እንዲጠብቅ መደረግ ያለበት መሆኑ በመታመኑ፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ እውጥቷል፡፡