የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት በደንብ ቁጥር 141/2000 የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን ዓላማውም የባቡር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት በመዘርጋት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ማካሄድ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካትና ከግብ ለማድረስ ድርጅታዊ አካላቱ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት በብቃትና በጥራት ማከናወን እንዲችሉ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት ለመፍጠር፣ ቀልጣፋና ፈጣን የሥራ እንቅስቃሴ ለማድረግ፣ ተገቢውን ሠራተኛ በተገቢው ቦታ በመመደብ ብቃትና ልምድ ያላቸው ሠራተኞችን ማፍራትና በአሰሪውና በሠራተኛው መካከል ያለው ግንኙነት ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የኢንዱስትሪ ሰላም በመፍጠር የመ/ቤቱ ዕቅዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ ለማስቻል የአስተዳደር መመሪያ መቅረጹ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፣
የአስተዳደር መመሪያው የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅን ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 494/1998ን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቷል ፡፡