የመመሪያ መለያ: 410/2013
ቀን: የካቲት 1፥ 2010 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት የተሻሻለ የትምህርትና ስልጠና አፈጻፀም መመሪያ ቁጥር 410/2013

የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ ልማት የሚወሰነዉ የሰዉ ሀይላቸዉን ለማብቃት በሚያወጧቸውና በሚተገብሯቸው የአቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችና ስልቶች ላይነው፡፡ በመሆኑም በሃገራችን የሚካሄዱ የሰው ሃብት አቅም ግንባታ ስራዎች በአጭር ጊዜ ወደ መካከለኛ ኢኮኖሚ እና በረጅም ጊዜ ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር ለተያዘው ሃገራዊ ራዕይ ስኬት ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ እንደሚገልጸው የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሰለጥኑ የሚደረገው የሥራ ችሎታቸውን አሻሽለው በተመደቡበት ሥራ ላይየተሻለ የሥራ ውጤት ለማስገኘት እንዲቻል ወይም በሙያ መሰላል ላይ ተመስርቶ ለበለጠ ኃላፊነት የሚያበቃቸው ዝግጅት እንዲኖራቸው ነው፡፡

በመሆኑም የኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማረጋገጥ፣ ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ከወቅቱ ተለዋዋጭ ጉዳዮች ጋር የሚራመድ እና ቀጣይነት ያለው ለውጥን ማረጋገጥ የሚችል አመራር እና ሠራተኛ መፍጠር የአቅም ግንባታ ስራዎች ማጠንጠኛ ነጥብ ነው፡፡ በዚህ ቅኝት የኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት የተጣለበትን ሃገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት እንዲችል፣ ከዓለም ዓቀፍ ደረጃዎች ጋር በማመጣጠን የከይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን ሃገራዊ ለማድረግ እና የልሕቀት ማዕከልነቱን ለማረጋገጥ የአመራሮች እና ሰራተኞች አቅም በተከታታይለመገንባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

እነዚህ የአቅም ግንባታ ስራዎች በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚሰጡ ሲሆን ለአብነትም ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ጋር በተደረገው ስምምነት ለአመራርና ሰራተኞች በሁለተኛ ዲግሪ በከይዘን የሚሰጠውን ሥልጠና ማንሳት ይቻላል፡፡ ከዚህ ባለፈ በአጋር አካላት የሚሰጡ የትምህርትና ሥልጠና ዕድሎችን በመጠቀም ለኢንስቲትዩቱ አቅም የሚሆኑ ልምዶችና ሥልጠናዎች በመገኘት ላይ ናቸው፡፡ ይህ የአቅም ግንባታ ስራ የሚመራበት ወጥ የሆነ እና ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ክፍተት በመኖሩ በሂደቱ ችግሮች ሲያጋጥሙ ቆይተዋል፡፡

በቀጣይ ይህንን ችግር ለመቀነስ የሚያስችል እና ግልጽ የሆነ የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት ኢንስቲትዩቱን በምስራቅ አፍሪካ የከይዘን ፍልስፍና የልህቀት ማዕከል የሚሆንበትን ራዕይለማሳካት የሚያስችል ስራ መሥራት ይገባል፡፡

በመሆኑም ኢንስቲትዩታችን በደንብ ቁጥር 256/2004 ተቋቁሞ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በኢንስቲትዩቱ ተመድበው በመሥራት ላይ የሚገኙት ሠራተኞች/ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች በፍልስፍናው ጊዜው የሚጠይቀውን ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙና የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም እንዲያዳብሩ እንዲሁም የልህቀት ማዕከልነት ራዕዩን ማሳካት የሚችልበትን ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ለማድረግ የትምህርትና ሥልጠና አፈፃፀም መመሪያ ተሻሽሎ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት

Ethiopian Kaizen Institute

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration