የመመሪያ መለያ: 116/2014
ቀን: ጥር 18፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኢንተርፕራይዝ ወይም ኢንዱስትሪ ገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 116/2014

መንግሥት የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ዘርፍ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመቅረጽ ለስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ ዕድልን በመፍጠርና በከተማችን የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት የተደራጁ ዜጎችን የገበያ ድጋፍ በመስጠት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተደራጅተው የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንዱስትሪዎች የውጭ ምርት እንዲተኩና በገበያው ላይ የሚታየውን የአቅርቦት ችግርበመቅረፍ ለከተማዋ ነዋሪ ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርትና አገልግሎት እንዲያቀርቡ እገዛ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ በመታመኑ፤

በተለያዩ የስራ ዘርፍ ተደራጅተው ወደ ሥራ የሚገቡ ነዋሪዎች በአካባቢ፣በክልልና በውጭገበያ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የድጋፍ ሥርዓት በመዘርጋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ የሚገኝ ቢሆንም እስካሁን ያለው የገበያ ድጋፍ አሰጣጥ ሁኔታ የኢንተርፕራይዞችን ብቃትና ተወዳዳሪነት የማያበረታታና ውስን ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚያሳትፍ የነበረ በመሆኑ፤

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን አገልግሎቶች ኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንዱስትሪዎች ከሚፈልጉት ድጋፍ አንፃር ፍትሃዊነት የጎደለው፤ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሌለው፤ የኢንተርፕራይዞችን ወይም ኢንዱስትሪዎችን ምልልስ የሚጨምር፤ ለብልሹ አሠራር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር ከመፍጠር አንፃርክፍተት የነበረበት በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ወጥነት ያለው አሠራርለመዘርጋት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration