አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ መሰል የሚዲያ ተቋማት ጋር ተፎካካሪ እንዲሁም ተመራጭ የሚዲያ ተቋም ለመሆን ዘመኑን የሚመጥን የስትራቴጂክ ዕቅድ እና መዋቅር መንደፍ አስፈላጊ በመሆኑና፤
ከዚህ ቀደሞ የነበረው የተቋሙን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በማሻሻል ይህን ዕቅድ የሚመጥን መዋቅራዊ አደረጃጀት እና የደመወዝ ስኬል ጥናት በማድረግ በስራ አመራር ቦርድ እንዲፀድቅ በመደረጉ፤
በፀደቀው የተቋሙ አደረጃጀት እና የደመወዝ ስኬል መሠረት የለውጥ ሂደቱን መሸከም እና ማስቀጠል የሚችል ትክክለኛ የሰው ኃይል በትክክለኛ ቦታ ወጥ በሆነ መመዘኛ በመጠቀም መደልደል ይቻል ዘንድ ለተቋሙ በደንብ ቁጥር 5/2012 በአንቀጽ 27(1)(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህ የድልድል የአፈፃፀም መመሪያ ወጥቷል