የመመሪያ መለያ: 1034/2017
ቀን: ታኅሣሥ 13፥ 2017 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል ሙሌት ስርዓት ረቂቅ መመሪያ ማብራሪያ መመሪያ ቁጥር 1034/2017

ከውጭ በሚገቡ ነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶች ላይ ያለውን መተማመን መቀነስ እና የተስፋፋውን የንግድ ሚዛን መዛባት ለመቅረፍ በትራንስፖርት ውስጥ የአገር ውስጥ ታዳሽ የኃይል ሀብቶችን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በተለይም በከተሞች ውስጥ በሰው ልጅ ጤና ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድር መልኩ በመንገድ ትራንስፖርት ውስጥ ከነዳጅ አጠቃቀም አኳያ የአየር ብክለትን መቀነስ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ከትራንስፖርት የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት በመቀነስ የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ቃል ኪዳንን ለማሟላት አስፈላጊ አካል በመሆኑ፤
ለመንገድ ትራንስፖርት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ስራ ላይ ለማዋል ከላይ የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ሰፋ ባለ መልኩ በማስገባት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ስርዓቶች መኖር እና ተደራሽነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፤
በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ የሃይል ሙሌት መሰረተ- ልማት ተከላ እና አገልግሎት ንግድ ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዝቅተኛ የፈቃድ መስፈርቶችን እና ደረጃን መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ የሃይል ሙሌት ጣቢያዎች እና ለኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ባለቤቶች ተመጣጣኝ የሃይል ሙሌት ታሪፍ ተመን ማውጣት በማስፈለጉ፤
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 810/2006 አንቀጽ 40(2) እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢነርጂ ደንብ ቁጥር 447/2011 አንቀጽ 82 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል ሙሌት ስርዓት መመሪያ ተዘጋጅቶ ለዉሳኔ ቀርቧል፡፡
ይህ ረቂቅ መመሪያ ሲዘጋጅ አዲስ ዘርፍ ከመሆኑ አንፃር ጉዳዩን በመመርመር፣የቁጥጥር ስራዉን በማሻሻል የዘርፉን ልማት እንዲያሳድግ ታስቧል፡፡ በዚሁ መሠረት ረቂቅ መመሪያዉ 7 ክፍሎች ፣ 22 አንቀጾች እና ሁለት አባሪዎች ያሉት ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን

Petroleum and Energy Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration