የመመሪያ መለያ: 562/2013
ቀን: ጥር 1፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የፍልሰት ተጎጅዎች ብሔራዊ የቅብብሎሽ ሥርዓት ረቂቅ መመሪያ ቁጥር 562/2013

ተጎጂዎችን ስለማዳን፣ ስለመመለስ፣ መልሶ ስለማቋቋም፣ ልዩ ልዩ ድጋፍ ስለሚያገኙበትና ከህብረተሰቡ ጋር ሊቀላቀሉ ስለሚችሉበት ሁኔታ ያለው አሠራር ግልጽነት የሚጎድለው፣ ሰፊ ክፍተት ያለበት እና ቅንጅታዊ አሠራርን ያልተከተለ በመሆኑ፤

ተጎጂዎችን በማዳን፣ በመመለስ፣ መልሶ በማቋቋም፣ ልዩ ልዩ ድጋፍ በማድረግና ከህብረተሰቡ ጋር በማቀላቀል ሂደት ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላትን እና የሚኖራቸውን ሚና በግልጽ መለየት እና ዝርዝር አሰራራቸውን መወሰን በማስፈለጉ፤

ተጎጂዎችን በማዳን፣ በመመለስ፣ መልሶ በማቋቋም፣ ልዩ ልዩ ድጋፍ ስለሚያገኙበት፣ ከህብረተሰቡ ጋር ሊቀላቀሉ ስለሚችሉበት ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በባለድርሻ አካላት መካከል የሚኖረውን የተጎጅዎች የቅብብሎሽ ሥርዓት እና የቅብብሎሽ ሥርዓቱ የሚሸፍናቸውን ጉዳዮች በዝርዝር መወሰን በማስፈለጉ፤

ብሔራዊ ምክር ቤቱ በሰዎች የመነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀጽ 34 (2) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የፍልሰት ብሔራዊ የትብብር ጥምረት

National Council on Migration

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration