የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የልማት ድርጅቶችን በበላይነት የማስተባበርና የመምራት እንዲሁም የመቆጣጠር ኃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ፤
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና ኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አሠራርን በመከታተል፣ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ግልጽነትና ተጠያቂነትን በተላበሰ መንገድ ለመተግበር የሚያስችል አንዱ መንገድ አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የዲስክሎዠር አፈጻጸም ስርዓት ወጥና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የልማት ድርጅቶች አፈፃፀም ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በታወቀ አሠራር መረጃቸውን ይፋ ማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን እና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት የሚያጠናክርና እምነት የሚያስገኝ በመሆኑ፤
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ቁጥር 445/2011 አንቀጽ (5) ንዑስ አንቀጽ (3) በተሰጠው ስ6 5 መሠረት ይህንን የዲስክሎዠር አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል፡፡