የመመሪያ መለያ: 408/2013
ቀን: ነሐሴ 1፥ 2000 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችና ቁሳቁሰች ጥናት፣ አፈቃቀድ እና አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 408/2013

የሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት አጠባበቅ ከሥራ ጋር የተያያዙ የጤንነትና የደኅንነት አጠባበቅ ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን፣ ዓላማውም የሠራተኞችን ደኅንነትና ጤንነት በመጠበቅ የሥራ ብቃት ማጐልበት፣ የሥራ ቦታን ለሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት በሚስማማ መልኩ ማዘጋጀት፣ ማደራጀት፣ ማሻሻልና መጠበቅ እን ዲ ሁም መሥሪያ ቤቱ /ተቋሙ/ በጐ በሆነ ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ተመስርቶ አመርቂ የሥራ ውጤት እንዲ ያስመዘግብ ማብቃት ነው፡፡

የሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት አጠባበቅ በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 47-56 ተደንግጓል፡፡ አሁን በሥራ ላይ ያለው የተሻሻለው የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች የሥራ ል ብስና መሣሪያ ዝግጅትና አሰጣጥ መመሪያ በጠባቡ በሥራ ልብስና መሣሪያዎች አፈቃቀድና አሰጣጥ ላይ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ከዚህ ሰፋ ባለ ሁኔታ ሳይንሳዊ ፅንሰ ሀሳቦች ላይ ተመስርቶ የሥራ አካባቢ ደኅንነትና ጤንነት አጠባበቅ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ካለመሆኑም ባሻገር በአዋጁ የተገለፁትን ድንጋጌዎች ለመፈፀም የሚያስችል አይደለም፡፡

ስለዚህ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 48 ንዑስ አንቀጽ 1/ለ/ መሥሪያ ቤቶች የሥራ አካባ ቢ ደኅንነትና ጤንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችና ቁሳቁሶችን ፍላጐት ለሠራተኞች እንዲ ያቀርቡና ስለአጠቃቀማቸው መመሪያ እንዲ ሰጡ በተደነገገው መሠረት ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

FDRE Civil Service Commission

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration