የመመሪያ መለያ: 8/2012
ቀን: ነሐሴ 4፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚ ደንበኞች የራሳቸውን አማራጭ የውሃ መገኛዎችን አጎልብተው እንዲጠቀሙ የሚያስችል መመሪያ ቁጥር 8/2012

ባለስልጣኑ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሚያቀርበውን ንጹህ የመጠጥ ውሃ በጥራትና በመጠን በማሳደግ ስርጭቱን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በከተማው መስፋት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት የውሃ ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ያለዉን ውስን የውሃ ምርት ለከተማዉ ነዋሪ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማከፋፈል በማስፈለጉ፡፡

በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በተቋቋመው ዴሊቨሪ ዩኒት በከተማው ውስጥ የሚስተዋለዉን የውሃ እጥረት ችግር ለመፍታት ባለስልጣኑ ለከፍተኛ ውሃ ተጠቃሚዎች የሚቀርበዉን የውሃ መጠን በመቀነስ ወደ ህዝቡ የሚሰራጨዉን የውሃ መጠን እንዲጨምር ማድረግ ያለበት መሆኑ በመታመኑ፡፡

ባለስልጣኑ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሚያቀርበዉን ንጹህ ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማሰራጨት እንዲችል ለከፍተኛ ውሃ ተጠቃሚዎች የሚያቀርበዉን የውሃ መጠን በመቀነስ ወደ ህዝቡ የሚሰራጨዉን የውሃ መጠን ለመጨመር ይረዳው ዘንድ ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚ ደንበኞች የራሳቸዉን አማራጭ የውሃ መገኛ እንዲያጎለብቱ እና እንዲጠቀሙ ማድረጉ ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑ ስለታመነ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

Addis Ababa Water and Sewerage Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration