የመመሪያ መለያ: 44/2013
ቀን: ግንቦት 2፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የተሸከርካሪ የደህንነት ቀበቶ በተሸከርካሪ ወንበሮች ላይ እንዲኖር እና ተግባራዊ እንዲደረግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 44/2013

የመንገድ ትራንስፖርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የማይተካ ሚና እንዳለው የሚካድ አይደለም። ሚናውንም ደህንነቱ የጠበቀ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈና በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ የተቀመጠ መሆን ይኖርበታል። ከነዚህ መንገዶች ውስጥ በማንኛውም እንቅስቃሴ የደኅንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን መጠቀም ወሳኝ ነው። የአለም የጤና ድርጅት እንዳወጣው መረጃ በሕዝብ ትራንስፖርት አማካኝነት የሚንቀሳቀስ አካላት በጉዞ ወቅት የደኅንነት ቀበቶ በአግባቡ ቢጠቀሙ አደጋ በሚያጋጥማቸው ወቅት አሽከርካሪውና ከፊት የሚቀመጡ አካላት ከ45 እስከ 50% ለሞት ተጋላጭነታቸውን እንደሚቀንስና ከኃላ የሚቀመጡ ተጓዦች ደግሞ ከ25 እስከ 35% ከሞት ሊታደጋቸው እንደሚችል ያሳያል። በሃገረችንም በደኅንነት ቀበቶ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች ጥናት ተደርጎባቸው የተቀመጡ ባይሆኑም ለአደጋዎቹ አስከፊነት የደኅንነት ቀበቶን አለመጠቀም ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የማይካድ ነው።

በደንብ ቁጥር 208/2003 እና በማሻሻያው 395/2009 ተራ ቁጥር 5 ጠቅላላ የጥንቃቄ መርሆች አንቀጽ ቁጥር 3 ከ ሀ እስከ ሐ እንዳስቀመጠው ማንኛውም አሽከርካሪ ከሞተር ብስክሌት በስተቀር የደኅንነት ቀበቶ ሳያስር በመንገድ ላይ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ማሽከርከር እንደሌለበት፤ ማንኛውም አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ወቅት በተሽከርካሪው ውስጥ የተሳፈረው ሰው የደኅንነት ቀበቶ ማሰሩን ማረጋገጥ እንዳለበትና በንዑስ አንቀጽ ለ (ማንኛውም አሽከርካሪ በሚያሽከረከርበት ወቅት በተሽከርካሪው ውስጥ የተሳፈረው ሰው የደኅንነት ቀበቶ ማሰሩን ማረጋገጥ እንዳለበት) ድንጋጌ ተፈፃሚ የማይሆንባቸው ተሽከርካሪዎችን በሚመለከት ባለስልጣኑ እንደሚወስን ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም የደኅንነት ቀበቶ ባለማሰር ምክንያት የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከልና ለመቀነስ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ይህንን መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Transport Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration