የግል መገልገያ ዕቃዎች ወደ ሀገር የሚገቡበትን ሁኔታ የሚወስነው በሥራ ላይ ያለው መመሪያ ለሕገ ወጥ ንግድ በር የከፈተ እና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ዓለምአቀፍ አሠራሮችን በተከተለ አኳኋን መመሪያውን አሻሽሎ ማውጣት በማስፈለጉ፤
በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (በአዋጅ ቁጥር 1160/2011 እንደተሻሻለው) አንቀጽ 33(2) የግል መገልገያ ዕቃዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር የሚገቡበት እና ከሀገር የሚወጡበትን ሁኔታ እንዲወስን ለገንዘብ ሚኒስቴር ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ፤
የገንዘብ ሚኒስቴር የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል፡፡