የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ብዛት በፍጥነት እያደገ በመሆኑና የከተማዋ ብሔራዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ተፈላጊነትና ተመራጭነት በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ የባለስልጣኑ ተግባርና የስራ እንቅስቃሴ ይበልጥ እየጨመረ እና እየተወሳሰበ በመሄዱ፤ ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከመፀዳጃ ቤቶች ጉድጓድ ፍሳሽ በተሸከርካሪ መሰብሰብ፣ በማጓጓዝና በማስወገድ ተግባር ላይ የግል የፍሳሽ በተሸከርካሪ አንሺ ባለንብረቶችን በማሳተፍ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ችግሮች በዘለቄታዊነት ለመፍታት አገልግሎት አሰጣጡን ግልፅ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ በማስፈለጉ፤
በግል ፍሳሽ በተሸከርካሪ አንሺዎች የፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ለመወሰንና የአገልግሎት ታሪፍ ለመቆጣጠር እና ወጥነት ያለው የአሠራር ስርዓት ለመዘርጋት ማንኛውም ስለግል ፍሳሽ በተሸከርካሪ የማንሳት አገልግሎት የሚሰጡ ውሳኔዎች እና አገልግሎቶች የሚመለከታቸው አካላት ግልፅ ለማድረግ በማስፈለጉ፤
በግል ፍሳሽ ማንሳት ስራ ቀልጣፊና ውጤታማ ለማድረግ በማህበር ተደራጅተው የሚመጡ አካላትን ለማበረታታት፣ ለተገልጋዮ ህብረተሰብ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት በመስጠት ግልፅነትና ተጠያቂነት ለማስፈን፣ የፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡