በዝውውር ሊይ የሚገኙ ሕጋዊ የገንዘብ ኖቶች በሥራ ላይ ከዋለ ረጅም ጊዜ የተቆጠረ ስለሆነ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች ሕትመት እና ስርጭት እየተጋለጡ በመሆኑ፣
የተሻሻለ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክቶችን በኖቶቹ ላይ በማድረግ የአገሪቱ ሕጋዊ የገንዘብ ኖቶችን የጥራት ደረጃ በማሻሻል የሀሰተኛ ገንዘብ ሕትመት እና ስርጭት ወንጀልን መከላከል በማስፈለጉ፣
ሕብረተሰቡ ለትላልቅ የገንዘብ ኖቶች ያለውን ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የባለ 200 ብር ኖት በማሳተም እና የገንዘብ አቅርቦትን በማሻሻሌ የህብረተሰቡን ፍላጎት ማርካት አስፈሊጊ በመሆኑ፣
ከባለ 5 ብር በስተቀር በአሁኑ ጊዜ በዝውውር ላይ የሚገኙ የገንዘብ ኖቶችን ባንኩ በሚያሳትማቸው አዳዲስ የገንዘብ ኖቶች ሙለ በሙለ በመቀየር የገንዘብ አጠቃቀምን ማሻሻል አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ (እንደተሻሻለ) አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 5(1)፣ 18(2) እና 27 (2) በተሰጠው ሥሌጣን መሠረት የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል፡፡