የመመሪያ መለያ: 970/2015
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ቦርድ ይግባኝ ስነ ስርአትና አሰራርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 970/2015

በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 7 የተመለከተው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ቦርድ በአዋጁ አንቀጽ 9(2) ዋና ዳይሬክተሩ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ በአዋጁ መሠረት የሚቀርቡ ይግባኞችን ተቀብሎ የማየትና የመወሰን ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ፤

በአዋጁ አንቀጽ 57(3) ፣ 59(5) ፣70 (2) ፣77 (5) እና 78 (4) መሠረት በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የሚሰጡ ውሳኔዎች ዙሪያ የሚቀርብለትን ይግባኝ ለመስማት የአሠራር ሂደት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የቀረበለትን የይግባኝ አቤቱታ ጉዳይ የሚመረምር ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ እንደሚሰይም የተደነገገ በመሆኑ፤

በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የባለስልጣኑ ቦርድ የቀረበለትን የይግባኝ አቤቱታ የሚመረምር ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ አሠራር የሚወስን መመሪያ እንደሚያወጣ በመደንገጉ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በአዋጁ አንቀጽ 89 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡


Whereas, the board established in accordance to article 7 of the proclamation 1113/2019 has the power to hear appeals against the decision given by the Director General of the authority based on the article 9 (2) of the same proclamation.

Whereas, it is necessary to issue rules of procedure for the Authority for Civil Society Organization’s Board that has the power to hear appeals from the decisions given by the Director-General by virtue of Articles 57(3), 59(5), 70(2), 77(4) and 78(4) of the same the Proclamation;

Whereas, according to sub-article 2 of Article 9 of the Proclamation, the Board shall, when necessary, set up an independent complaint review committee to conduct an investigation into the appeal brought to it;

Whereas it is found necessary to issue a directive to implement the above-mentioned. Therefore, the Authority for Civil Society Organizations has issued the following Directive in accordance to the powers conferred on it by virtue of Article 89(2) of the Proclamation.

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስልጣን

Authority for Civil Society Organizations

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration