የመመሪያ መለያ: 48/2013
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአደራ ቤተሰብና የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 48/2013

ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ያጡና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ህጻናትን በተለያዩ አማራጭ የድጋፍና እንክብካቤ ዘዴዎች ሊደገፉ እንደሚገባ በኢፌዴሪ ህገ መንግሥት እና በሌሎች ዝርዝር ህጎች መንግሥት የገባውን ቃል ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል የአደራ ቤተሰብንና የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ አገልግሎት የአሠራር ስርዓትን ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ጉዲፈቻ የሚፈጸምባቸው መሠረታዊ መርሆዎች የተቀመጡ ቢሆንም ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ባለመኖሩ በአሰራሩ ላይ ወጥነትና ቅንጅታዊ አሠራር የጎደለው ሆኖ በመታየቱ አሰራሩ ሕግን የተከተለ፣ ወጥነት ያለውና ቅንጅታዊ አሰራሩ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚወስን መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፣

ኢትዮጵያ ተቀብላ ያጸደቀቻቸው የዓለም ዓቀፍ የሕፃናት መብት ኮንቬሽን እና የአፍሪካ የህጻናት መብትና ደኅንነት ቻርተር የአደራ ቤተሰብና የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ በተመለከተ ያስቀመጡትን ድንጋጌዎች በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የሚስችል መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በአገር ውስጥ ጉዲፈቻ አፈጻጸም ያለውን የአሠራር ችግር ለማስወገድ የሚያስችል ጠንካራ የሆነ የክትትልና ድጋፍ የአሠራር ስርዓት መዘርጋት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፣

የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ይህንን የአደራ ቤተሰብና የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ የአፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር

FDRE Ministry of Women Children and Youth

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration