የመመሪያ መለያ: 976/2016
ቀን: ጥር 21፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

አማራጭ የህፃናት ድጋፍና ክብካቤ መመሪያ ቁጥር 976/2016

በኢትዮጵያ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ በሆኑ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡና በተለያዩ አማራጭ የሕፃናት ድጋፍና ክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ለእነዚህ ሕፃናት ደረጃውን የጠበቀና ሁሉን አቀፍ የሕፃናት ድጋፍና ክብካቤ ዘዴዎች ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

አሁን በስራ ላይ የሚገኙ አማራጭ የድጋፍና ክብካቤ ዘዴዎች በተለያዩ ሰነዶች ውስጥ ተካተው የሚገኙ በመሆናቸው ለአስፈጻሚ አካላት ለአፈጻጸም አስቸጋሪ ከመሆናቸውም በላይ የሕግ አስገዳጅነት የሌላቸው በመሆናቸው አንድ ወጥ የሆነና አስገዳጅነት ያለው የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፌዴራል የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 19 (4) እንዲሁም አንቀጽ 36 (አ) እና (ኸ) በተሰጠው ሕግ የማመንጨትና የማስፈጸም ሥልጣን መሠረት ደረጃውን የጠበቀ አማራጭ የሕፃናት ድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ይህን መመሪያ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

Addis Ababa City Administration Women, Children and Social Affairs Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration