በፌዴራል የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሥራ መሪዎች የተለያዩ ክፍያዎች ስርዓት ባለመኖሩ ወይም በወጥነት ባለመተግበሩ፣ጥቅማ ጥቅሞችና ይህም ብቃት ያላቸውን የሥራ መሪዎችና ባለሞያዎችን ወደ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ለመሳብና ለማቆየት ባለማስቻሉ፣
በመንግሥት መደበኛ በጀት የሚተዳደሩ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ መሪዎችን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችና ክፍያዎችን ወጥነትና ተመሳሳይነት ባለው ሁኔታ በጥናት ላይ ተመስርቶ እስታንዳርዳይዝድ ማድረግና የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በሌላ በኩል የፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ (4) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአበል ዓይነቶችንና ክፍያዎችን እያጠና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም አፈፃፀማቸውን ይከታተላል በሚልበመደንገጉ፣
ኮሚሽኑ በፌዴራል የመንግሥት ረራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 156(2) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡