የመመሪያ መለያ: 1111/18
ቀን: መስከረም ፥2018 ዓ.ም.
Language: Amharic

የመንግሥት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1111/2018

በሥራ ላይ ያለው የመንግሥት ሠራተኞች የቀን የውሎ አበል ተመን በሥራ ላይ ከዋለ ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በክልሎች፣ በዞንና በወረዳ ከተሞች የሚገኙ ሆቴሎች ከሚያስከፍሉት የምግብና የመኝታ ዋጋ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ለመስክ ሥራ በሚወጡ ሠራተኞች ላይ ከፍተኛ የወጪ ጫና በማሳደር በመስክ ሥራ ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከማሳረፉም በላይ የሥራ ተነሳሽነትን በመቀነስ ለቅሬታና አቤቱታ ምክንያት በመሆኑ፣

በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ (4) የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሸን የአበል ዓይነቶችንና ክፍያዎችን እያጠና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም አፈፃፀማቸውን ይከታተላል በሚል በመደንገጉ፣

በሌላ በኩል የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብቁጥር 502/2014 አንቀፅ 4 ንዑስ አንቀፅ 14 ብቃት ያላቸውን የሥራ መሪዎችና ባለሞያዎችን ወደ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ለመሳብና ለማቆየት የሚያስችል የክፍያ ሥርዓት እንዲኖር በየወቅቱ እያጠና ለመንግሥት ውሳኔ ያቀርባል፣ ሲፈቀዱም አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል በሚል በመደንገጉ፣

ኮሚሽኑ በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 156 (2) መሠረት ለአፈጻጸም እንዲመች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይህን መመሪያ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

FDRE Civil Service Commission

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration