በሥራ ላይ ያለው የመንግሥት ተሿሚዎች የቀን የውሎ አበል ተመን በሥራ ላይ ከዋለ ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ በመሆኑ፣
በአሁኑ ወቅት በክልሎች፣ በዞንና በወረዳ ከተሞች የሚገኙ ሆቴሎች ከሚያስከፍሉት የምግብና የመኝታ ዋጋ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ፣
ለመስክ ሥራ በሚወጡ ተሿሚዎች ላይ ከፍተኛ የወጪ ጫና በማሳደር በመስክ ሥራ ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከማሳረፉም በላይ የሥራ ተነሳሽነትን በመቀነስ ለቅሬታና አቤቱታ ምክንያት በመሆኑ፣
በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ (4) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአበል ዓይነቶችንና ክፍያዎችን እያጠና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም አፈፃፀማቸውን ይከታተላል በሚል በመደንገጉ፣
ኮሚሽኑ በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 156(2) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል።