የባለሥልጣን መ/ቤቱን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሥልጣን፣ ተግባር እና ኃላፊነት ለመወሰን እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የአሠራር ሁኔታ፣ በጀት አጠቃቀም፣ የስራ ግንኙነትና የስራ አፈፃፀም መዘጋጀት የባለስልጣኑን የስራ አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ እንደሚያፋጥን በመታመኑ፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።